የእርስዎ መረጃ
መለያዎን ይሰርዙ
የZemeromo መለያዎን ራስዎ በመተግበሪያው ውስጥ መሰረዝ ይችላሉ። መሰረዙ ሊቀለበስ አይችልም።
ይህ ትርጉም ነው። በዚህ ጽሑፍና በእንግሊዝኛው መካከል ልዩነት ቢኖር የእንግሊዝኛው ቅጂ ይገዛል።
እንዴት እንደሚሰርዙት
- የZemeromo መተግበሪያን ይክፈቱና ይግቡ።
- ወደ «ቅንብሮች» ይሂዱና «መለያ ሰርዝ»ን ይምረጡ።
- የሚሆነውን ያንብቡ፣ ለማረጋገጥ መተግበሪያው የሚጠይቀውን ቃል ይጻፉ፣ ከዚያ «መለያዬን ሰርዝ»ን ይንኩ።
የሚሰረዘው
- ስምዎ፣ የተጠቃሚ ስምዎ፣ ፎቶዎና መግለጫዎ።
- ኢሜይልዎና መግቢያዎ፤ ተመልሰው መግባት አይችሉም።
- የወደዷቸው፣ የሚከተሏቸው ሰዎች፣ እና በእርስዎና በማድመጥ ታሪክዎ መካከል ያለው ትስስር።
- የቡድን አባልነቶችዎ።
የሚቀመጠው
- የግዢ መዝገቦች፣ ስምዎ ተወግዶ። ዘማሪያን የሚከፈላቸው ከእነዚህ ስለሆነ ሊሰረዙ አይችሉም።
ቡድን የሚመሩ ከሆነ
መለያዎን ከመሰረዝዎ በፊት የአስተዳዳሪነት መብትን ለሌላ አባል ያስተላልፉ፣ ወይም ቡድኑን ይሰርዙ። ይህ የሚያስፈልጋቸውን ቡድኖች መተግበሪያው ይነግርዎታል።
ዘማሪ ከሆኑ
የዘማሪ መለያዎች የሚዘጉት በጥያቄ ነው፤ መዝሙርዎ፣ ገቢዎና ካርዶችዎ መጀመሪያ እንዲጠናቀቁ። በመተግበሪያው «እንዲሰረዝ ጠይቅ»ን ይምረጡ፤ ይህ እንዳለቀ መለያውን እንዘጋለን።
መግባት አልቻሉም?
መለያዎን ለመሰረዝ መግባት ካልቻሉ፣ በተመዘገቡበት የኢሜይል አድራሻ ያግኙን፤ እንረዳዎታለን።
ያግኙንለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም.